Loading...
Ethiopian This Week

የአማራና የትግራይ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች የሚሳተፉበት የሰላም ኮንፍረንስ በጎንደር ሊካሄድ ነው::

November 1, 2017 3:21 pm Published by
facebooktwittergoogle_plusmail

 

የአማራና የትግራይ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች የሚሳተፉበት የሰላም ኮንፍረንስ በመጪው ህዳር ወር መጀመሪያ በጎንደር ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የኮንፍረንሱን ዝግጅት አስመልክተው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየልኝ ሙሉዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ኮንፍረንሱ የሁለቱን ህዝቦች የቆየ ትስስርና መልካም ጉርብትና የሚያጠናክር ነው፡፡

በዚህም “ባለፈው ዓመት ትግራይ ላይ በተካሄደው የሰላም ኮንፍረንስ የተሳተፉ የሀገር ሽማግሌዎች ያሳለፉት ውሳኔ አፈጻጸም ይገመገማል” ብለዋል፡፡

በተለይም በጸገዴና በጠገዴ አጎራባች አካባቢዎች የወሰን አከላለል ተፈጻሚነትን በተመለከተ፥ የሁለቱ ክልሎች የሀገር ሽማግሌዎች ያሳለፏቸው ውሳኔዎች አተገባበር በኮንፍረንሱ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል፡፡

በሁለቱ ክልሎች የሰፈነውን ሰላም ቀጣይነት በማረጋገጥ ለዘመናት አብሮ የዘለቀውን ወንድማማችነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ኮንፍረንሱ ይመክራል ተብሏል፡፡

ብአዴንና ህወሐት የትግል አጋርነታቸውን ዳግም በማጠናከር የሁለቱ ክልል ህዝቦች ትስስር ተጠናክሮ እንዲቀጥል፥ ይበልጥ ተቀራርበው የሚሰሩበትን ምቹ ሁኔታ ከንፍረንሱ እንደሚፈጥርም ነው አቶ አየልኝ የተናገሩት፡፡

“አስተዳደሩ ለኮንፍረንሱ መሳካት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፥ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱንም አስታውቀዋል፡፡

የዞኑ ህዝብ እንግዳ ተቀባይነቱን ዳግም በማረጋገጥ በኮንፍረንሱ ወቅት ለሚመጡ እንግዶች ወንድማዊ አቀባበል በማድረግ፥ ለኮንፍረንሱ መሳካት የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በህዳር ወር መጀመሪያ በሚካሄደው የሰላም ኮንፍረንስ ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ ነባር ታጋዮችና አመራሮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡   Source ( ENA)

facebooktwittergoogle_plusmail
Tags: , , ,

Categorised in:

This post was written by ETW

Leave a Reply